አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን በደቡብ ዕዝ በምዕራብ አባያ ማሰልጠኛ ተቋም ያሰለጠናቸውን 599 ምልምል እና 63 መሰረታዊ ፖሊሶች በዛሬው ዕለት አስመርቋል።
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ እንዳሉት፤ አኩሪ የጀግንነት ታሪክ ያላት ኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ተከባብረውና ተዋደው የሚኖሩባት ናት።
ለዘመናት ሉዓላዊነቷን አስጠብቃ የኖረችውና የጥቁር ህዝቦች ኩራት የሆነችው ኢትዮጵያ፤ ለመበልፀግ የሚያስችሏትን ትላልቅ የልማት እቅዶችን አዘጋጅታ በመተግበር ዕድገትን ለማረጋገጥ እየተጋች ትገኛለች ብለዋል።
ክልሉ ልዩ ልዩ ባህልና የአኗኗር ዘይቤ፣ የከበሩ ማዕድናትን ያካተተ ለኢንቨስትመንትና ቱሪዝም እጅግ ተመራጭ መሆኑን ጠቅሰው፤ የክልሉ ሠላም እንዲጠበቅ የፖሊስ ተቋማትን ለማጠናከር እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
የፖሊስ ሙያ የተከበረ ስራ ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ ሙያው በሰብዓዊነትና በታማኝነት ህዝብን ለማገልገል መስዋዕትነት የሚከፈልበት መሆኑን አስገንዝበዋል።
የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ፍስሐ ጋረደው በበኩላቸው፥ ክልሉ ከተመሰረተመበት ጊዜ ጀምሮ ዘርፈ ብዙ የፖሊስ ተግባራት ተከናውነዋል ብለዋል።
የሚያጋጥሙ ችግሮችን በየደረጃው ካሉ የሕብረተሰብ ክፍሎች ጋር በመወያየትና አንፃራዊ ሰላም ማረጋገጥ መቻሉን አንስተዋል።
የፖሊስ ኃይልን ለማደራጀችና አሰራሩን ለማዘመን በተያዘው የሪፎርም እቅድ የአባላቱን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ሰፊና ክልላዊ እና ሀገራዊ ፋይዳ ያላቸው ፕሮጀክቶች እየተገበሩ እንደሆነ ተናግረዋል።
በታሪክነሽ ሴታ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!