አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአምራች ዘርፉ የሚስተዋሉ ማነቆዎችን ለመፍታት የተጀመረው የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የኢንዱስትሪዎችን ውጤታማነት እያረጋገጠ ነው አሉ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ።
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አመራሮች እና አባላት በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የቦሌ ለሚ ልዩ ኢኮኖሚ ዞንን ጎብኝተዋል።
አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ ጉብኝቱ የኢንዱስትሪዎቹን የሥራ እንቅስቃሴ እና ያሉበትን ደረጃ ለመመልከት ያለመ ነው።
በዘርፉ የሚስተዋሉ ማነቆዎችን ለመፍታት የተጀመረው የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የኢንዱስትሪዎችን ውጤታማነት እያረጋገጠ እንደሚገኝ መመልከታቸውን ጠቅሰዋል።
የአምራች ዘርፉ የውጭ ምንዛሪን በማዳን እና ሰፊ የሥራ እድል በመፍጠር ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን አመልክተዋል፡፡
የዘርፉን እድገት ለማረጋገጥ የተጀመሩ ሥራዎችን ማጠናከር እንደሚገባ ገልጸው ÷ለዚህም ምክር ቤቱ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል።
የምክር ቤቱ አመራሮች እና አባላት የኤ ኤም ጂ ሆልዲንግስን የሥራ እንቅስቃሴ መጎብኘታቸውም ተመላክቷል፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!