አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ2ኛ ሳምንት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ፋሲል ከነማ ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡
በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ የፋሲል ከነማን የማሸነፊያ ግቦች በረከት ግዛው እና አቤኔዘር ዮሀንስ አስቆጥረዋል፡፡
ፋሲል ከነማ ወደ ድል ሲመለስ ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ተከታታይ 2ኛ ሽንፈት አስተናግዷል፡፡
አዲስ አበባ ስታዲየም ላይ በተደረገ በሌላ የሊጉ ጨዋታ አዳማ ከተማ እና ሸገር ከተማ ያለምንም ግብ አቻ ተለያይተዋል፡፡
አዳማ ከተማ ተከታታይ 2ኛ ጨዋታውን በአቻ ውጤት ሲያጠናቅቅ ሸገር ከተማ ከሽንፈት መልስ የአቻ ውጤት አስመዝግቧል፡፡
በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም የሊጉ ጨዋታ ሲቀጥል ወላይታ ድቻ ከድሬዳዋ ከተማ ጨዋታቸውን እያደረጉ ይገኛል፡፡