አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በክረምቱ የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት ውሉ በመጠናቀቁ ከማንቼስተር ሲቲ ጋር የተለያየው ስኮት ካርሰን ጓንቱን መስቀሉን ይፋ አድርጓል፡፡
በማንቼስተር ሲቲ ቤት ስድስት ዓመታት መቆየት የቻለው ግብ ጠባቂው ስኮት ካርሰን በ40 ዓመቱ ነው ጓንቱን የሰቀለው፡፡
ስኮት ካርሰን በሲቲ በቆየባቸው 6 ዓመታት የፕርሚየር ሊግ እና የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግን ጨምሮ የተለያዩ ዋንጫዎችን ማሳካት ችሏል፡፡
ግብ ጠባቂው በማንቼስተር ሲቲ ቆይታው ሁለት ጨዋታዎችን ብቻ ያደረገ ሲሆን ÷ አንዱን ጨዋታ በሊጉ ቀሪውን አንድ ጨዋታ ደግሞ በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ማድረጉ ይታወሳል፡፡