አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዕድሜያቸው ከአምስት ዓመት በታች ለሆኑ ሕጻናት ታላሚ ተኮር የተቀናጀ ማካካሻ ክትባት በዘመቻ እየተሰጠ ነው።
በክልሉ ጤና ቢሮ የእናቶች እና ሕጻናት ጤናና ሥርዓተ ምግብ አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ሌጂሶ ለፋና ዲጂታል እንዳሉት ፥ የክትባት ዘመቻው ለተከታታይ 10 ቀናት ይሰጣል።
በዚህም ባለፉት 5 ዓመታት በተለያዩ ምክንያቶች ክትባት ያልጀመሩ 101 ሺህ 417፣ ጀምረው ያቋረጡ 93 ሺህ 695 እንዲሁም የኩፍኝ ክትባት ያልተከተቡ 193 ሺህ 309 ሕጻናት ክትባቱን እንደሚወስዱ ተናግረዋል።
በዘመቻው በርቀትና መልክዓምድር ምክንያት ክትባት ያልወሰዱ፣ በከተሞች ውስጥ በጎዳና እና በከተማ ዳርቻ የሚገኙ ሕጻናትን በማፈላለግ ክትባት እንደሚሰጥ አብራርተዋል፡፡
ከክትባቱ ጎን ለጎንም የሥርዓተ ምግብ ልየታ፣ የማሕጸን ውልቃት፣ የፊስቱላ እና የማሕጸን በር ካንሰር ሕመም ያለባቸው የሕብረተሰብ ክፍሎችን የመለየት ሥራ እንደሚከናወን አመልክተዋል፡፡
በአድማሱ አራጋው
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!