Law and Justice concept. Mallet of the judge, books, scales of justice. Gray stone background, reflections on the floor, place for typography. Courtroom theme.

ፍርድ ቤቱ አርቲስት ሀጫሉን በመግደል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር በዋሉት ግለሰቦች ላይ ፖሊስ ምርመራ እንዲያደርግ ተጨማሪ 10 ቀን ፈቀደ

By Tibebu Kebede

August 18, 2020

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 12፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) አርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳን በመግደል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉት ጥላሁን ያሚ እና አብዲ ዓለማየሁ ዛሬ ፍርድ ቤት የቀረቡ ሲሆን፥ ፍርድ ቤቱ ለፖሊስ 10 ቀን ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ፈቅዷል።

በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ተረኛ ችሎት ከዚህ በፊት አያያዛቸውን በተመለከተ የእስረኞች አስተዳደር ቀርቦ እንዲያብራራ ትእዛዝ መስጠቱን ተከትሎ ችሎቱ የምርመራ ውጤቱን ለመጠባበቅ የተሰየመ ሲሆን፥ ከእስረኞች አስተዳደር ግን ማንም ሰው ሳይገኝ ቀርቷል።