አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 14፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ማዕድን ኮርፖሬሽን እና የእንግሊዙ ኩባንያ ሰንበርድ ባዮ ፊውል አፍሪካ በታዳሽ ኃይል ዘርፍ በትብብር ለመስራት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል።
ስምምነቱን የኢትዮጵያ ማዕድን ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ቴዎድሮስ ጌታቸው እና የሰንበርድ ባዮ ፊውል አፍሪካ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሪቻርድ ቤኔት ተፈራርመዋል።
በስምምነቱ መሰረት ኮርፖሬሽኑ በታዳሽ ኃይል ዘርፍ በተለይም በአቪዬሽን ነዳጅ ልማት ከሰንበርድ ባዮ ፊውል አፍሪካ ጋር በትበብር የሚሰራ ይሆናል።
አቶ ቴዎድሮስ በወቅቱ እንዳሉት፥ በኢትዮጵያ በታዳሽ ኃይል ልማት የተጀመሩ ሥራዎች አበረታች ውጤት እያስመዘገቡ ነው።
የዛሬው ስምምነትም የታዳሽ ኃይል፣ አረንጓዴ ልማት፣ አቪዬሽን ነዳጅ እና ሌሎች የባዮ ኢነርጂ ዘርፎችን ለማጠናከር ያስችላል ነው ያሉት።
በኢትዮጵያ የሚገኙ የተፈጥሮ ሃብቶችን በሚገባ በመለየት ጥቅም ላይ ለማዋል በትኩረት እንደሚሰራም አመልክተዋል።
ሪቻርድ ቤኔት በበኩላቸው፥ ሰንበርድ ባዮ ፊውል በተለያዩ ሀገራት በዘርፉ ያካበተውን ልምድ በመጠቀም በኢትዮጵያ በታዳሽ ኃይል ልማት በቁርጠኝነት እንደሚሰራ ተናግረዋል።
በመላኩ ገድፍ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!