አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 14፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን በዘጋቢ ፊልም፣ ዜና እና በተለያዩ ፕሮግራሞች ላበረከተው አስተዋፅኦ ከአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማሕበራት ምክር ቤት ዕውቅና ተሰጠው።
ምክር ቤቱ በየዓመቱ የመገናኛ ብዙኃን ተቋማት ባለሙያዎችና አመራሮች የሚዲያ ሥራዎችን በተመለከተ የሚመካከሩበትን መድረክ የሚያዘጋጅ ሲሆን÷ የዘንድሮ ዓመታዊ የቻምበር – ሚዲያ ቀን “ሚዲያ – ለአረንጓዴ ልማት ተግባራት” በሚል መሪ ሐሳብ በትናንትናው ዕለት አካሂዷል።
የምክር ቤቱ ዋና ፀሐፊ መሠረት ሞላ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ የሚዲያ ባለሙያዎች በተለይም የንግድ እና ኢኮኖሚ ዘርፍ ጋዜጠኞች በዕውቀት እና በማስተዋል ከተንቀሳቀሱ ለሀገራዊ ንግድና ኢኮኖሚ ዕድገት የሚጫወቱት ሚና ከፍተኛ ነው።
የምክር ቤቱ የፖሊሲ፣ አድቮኬሲና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ካሳሁን ማሞ በበኩላቸው÷ ኢትዮጵያ እያስመዘገበች ካለው ፈጣን የንግድ እና ኢኮኖሚ ዕድገት ጋር የሚመጣጠን የቢዝነስ ዘገባ እንዲጎለብት ምክር ቤቱ ከሚዲያ ተቋማት ጋር በትኩረት እንደሚሰራ ተናግረዋል።
79 ዓመታትን ያስቆጠረው የአዲስ አበባ ንግድ ምክር ቤት (አዲስ ቻምበር) ከሚዲያ ተቋማት ጋር ለመስራት የሚያስችለውን ዝግጅት ማጠናቀቁንም አመላክተዋል።
በመድረኩ ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን በዘጋቢ ፊልም፣ ዜና እና በተለያዩ ፕሮግራሞች ላበረከተው አስተዋፅኦ ከምክር ቤቱ ፕሬዚዳንት ወ/ሮ ዘሐራ መሐመድ እጅ ዕውቅናና የምስክር ወረቀት ተቀብሏል።
በሺበሺ ዓለማየሁ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!