አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 14፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ እና ሞዛምቢክ በወታደራዊ መስኮች ያላቸውን የቆየ ትብብር ለማጠናከር ተስማምተዋል።
የመከላከያ ሚኒስትር አይሻ መሃመድ (ኢ/ር) ከሞዛምቢክ አቻቸው ሜጄር ጄኔራል ክሪስቶቫ አርቱር ቹሜን ጋር በጽ/ቤታቸው ተወያይተዋል።
በውይይቱ ወቅት ኢትዮጵያና ሞዛምቢክ ዘመን የተሻገረ ታሪካዊና ወታደራዊ ግንኙነት እንዳላቸው ያነሱት ሚኒስትሯ፤ በቀጣይ በልዩ ልዩ ወታደራዊ የትብብር መስኮች በጋራ ለመስራት ኢትዮጵያ ፍላጎት እንዳላት ተናግረዋል፡፡
ሜጄር ጄኔራል ክሪስቶቫ አርቱር ቹሜን በበኩላቸው፥ ሞዛምቢክ ከኢትዮጵያ ጋር ላላት ታሪካዊ ግንኙነት ትልቅ ሥፍራ እንደምትሰጥ ጠቁመዋል።
በተለይም ሽብርተኝነትን በመካላከል፣ በወታደራዊ ኢንዱስትሪ መስኮች፣ በበረራ ስልጠና እና ጥገና እንዲሁም በሳይበር ደህንነት መስኮች አብራ ለመስራት ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላት ገልጸዋል፡፡
በቅርቡም የልዑካን ቡድን ወደ ኢትዮጵያ በመላክ ጠንካራ ተቋማዊ ትስስርን የመፍጠር ስራዎች እንደሚሰሩ ማመልከታቸውን የመከላከያ ኦንላይን ሚዲያ ለፋና ዲጂታል ገልጿል።
በመላኩ ገድፍ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡- YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!