የሀገር ውስጥ ዜና

ባለፉት 3 ዓመታት የጎርፍ አደጋ በመከላከል ውጤታማ ስራ ተከናውኗል

By Yonas Getnet

October 24, 2025

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 14፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ባለፉት ሦስት ዓመታት በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የሚከሰተውን የጎርፍ አደጋ ለመከላከል የሚያስችል ውጤታማ ስራ ተከናውኗል አለ።

በኦሞ ጊቤ እና በስምጥ ሸለቆ ተፋሰሶች አካባቢ የሚከሰተውን የጎርፍ አደጋ በዘላቂነት ለመከላከል የሚያስችል የተፋሰስ ጥናት ለማካሄድ ሚኒስቴሩ ኤስደብሊውኤስ ከተባለ ዓለም አቀፍ ድርጅት ጋር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርሟል።

በፊርማ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) እንዳሉት፤ ኢትዮጵያ ለጎርፍ አደጋ መከላከልና ዝግጁነት የምታደርገው ጥረት የጎርፍ አደጋን በዘላቂነት ለመቀነስ ወሳኝ ሚና አለው።

በግብርና፣ በመሠረተ ልማት፣ በንብረት እና በሰው ሕይወት ላይ የጎርፍ አደጋ የሚያስከትለውን ጉዳት በሳይንሳዊ መንገድ በዘላቂነት ለመፍታት መንግስት በትኩረት እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

በዚህ ረገድ ከዓለም ባንክ ጋር በትብብር እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰው፤ የዛሬው ስምምነት የኢትዮጵያ የጎርፍ አደጋ መከላከልና ዝግጁነት ወደ ላቀ ምዕራፍ የሚያሸጋገር ነው ብለዋል።

ጥናቱ የጎርፍ አደጋን በዘላቂነት ለመቀነስ የሚያስችሉ የመፍትሄ ሀሳቦችን ያቀርባል ተብሎ እንደሚጠበቅ አብራርተዋል።

‎የኤስደብሊውኤስ ስራ አስኪያጅ ጃያን ካርሎ በበኩላቸው፤ የጎርፍ አደጋን መቀነስ የሚያስችል መፍትሔ ለማበጀት የሚያስችል ጥናት ለመስራት በትጋት እንደሚሰራ አረጋግጠዋል።

ጥናቱ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ እንደሚጠናቀቅ መጠቆሙን የሚኒስቴሩ የህዝብ ግንኙነት እና ኮሙኒኬሽን ስራ አስፈጻሚ ጌትነት ስሜ ለፋና ዲጂታል ገልጸዋል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!