አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 14፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ባለፉት ዓመታት ያየናቸው ፈተናዎች እና መከራዎች አጠንክረውን በበለጠ ጽናት ተግተን እንድንሰራ እና ውጤት እንድናገኝ አድርገውናል አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ‘የሚኒስትሮች ምክር ቤት ምልከታ በኮይሻ’ በሚል ርዕስ የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ 100 ቀናት የማክሮኢኮኖሚ አፈፃፀም ግምገማ ውይይት በኮይሻ ግድብ ከሚኒስትሮች ጋር አድርገዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በውይይቱ ላይ እንዳሉት፤ በለውጡ ዓመታት ትኩረት ከተሰጣቸው ስራዎች መካከል አንዱ ኢትዮጵያንና ጸጋዎቿን በሚገባ ማወቅ ነው።
ኢትዮጵያ የብልጽግና ጉዞዋን በማሳካት የሚገባትንም ስፍራ ትይዛለች በማለት ገልጸው፤ የኢትዮጵያን ብቃት እና አቅም በቅጡ መገንዘብ ሀገርን ለመስራት ቁልፍ ሚና እንደሚጫወት ጠቅሰዋል።
በዚህ ሂደት ውስጥ በርካታ አቅምን የሚገልጡ ስራዎች መከናወናቸውንም አመልክተው፤ በአብነትም የጨበራ ጩርጩራ ፓርክ እና ኮይሻ ፕሮጀክቶችን ጠቅሰዋል።
ሀገሩን የሚያውቅ እና በሀገሩ ክብር የሚሰማው ሰው ተግቶ ለመስራት እና እያንዳንዷን ቀን ለመለወጥ ዕድል አድርጎ እንደሚወስድ ተናግረዋል።
ባለፉት ዓመታት ያየናቸው ፈተናዎች እና መከራዎች አጠንክረውን በበለጠ ጽናት ተግተን እንድንስራ እና ውጤት እንድናገኝ አድርገውናል ብለዋል።
ኢትዮጵያ እንድምትበለጽግና የሚገባትን ስፍራ እንደምትይዝ ምንም ጥርጥር የለውም ነው ያሉት።
ይህን ራዕይ ለማሳካት የእያንዳንዱን ዜጋ ጥረት እና ድካም እንደሚጠይቅ በማመልከት፤ ተግተን ከሰራን በልጆቻችን ላይ ፍሬውን ለማየት ጊዜው ሩቅ አይደለም ብለዋል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!