አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 15፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ9ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሃ ግብር ዛሬ አራት ጨዋታዎች ይደረጋሉ፡፡
ምሽት 1 ሰዓት 30 ላይ ማንቼስተር ዩናይትድ በሜዳው ኦልድትራፎርድ ብራይተንን የሚያስተናግድበት ጨዋታ ይጠበቃል፡፡
ከረጅም ጊዜ በኋላ ተከታታይ ሁለት ጨዋታዎችን በሊጉ ያሸነፈው ማንቼስተር ዩናይትድ አሸናፊነቱን ለማስቀጠል ይፋለማል።
ሁለቱ ቡድኖች እርስ በርስ ካደረጓቸው ያለፉት አምስት ጨዋታዎች ብራይተን አራቱን በማሸነፍ የበላይነቱን የያዘ ሲሆን ማንቼስተር ዩናይትድ በአንዱ ድል አድርጓል፡፡
የቀያይ ሰይጣኖቹ አምበል ፖርቹጋላዊው ብሩኖ ፈርናንዴዝ 300ኛ ጨዋታውን በዩናይትድ ማልያ የሚያርግ ይሆናል፡፡
ምሽት 4 ሰዓት ላይ ሊቨርፑል ከሜዳው ውጪ ከብሬንትፎርድ ጨዋታውን ያደርጋል፡፡
ሊቨርፑል በሁሉም ውድድር ከተከታታይ አራት ጨዋታዎች ሽንፈት በኋላ በሳምንቱ አጋማሽ በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ በሰፊ የግብ ልዩነት ድል በማድረግ ወደ ድል መመለሱ ይታወቃል፡፡
በአሰልጣኝ አርኔ ስሎት የሚመራው ሊቨርፑል በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ያገኘውን ድል በሊጉ ለማስቀጠል የሚያደርገው ፍልሚያ ይጠበቃል፡፡
ከእነዚህ ጨዋታዎች አስቀድሞ ኒውካስል ዩናይትድ ከፉልሃም እንዲሁም ቼልሲ ከሰንደርላንድ በተመሳሳይ አመሻሽ 11 ሰዓት ላይ ይገናኛሉ፡፡
ትናንት ምሽት በተደረገ የ9ኛ ሳምንት የሊጉ ጨዋታ ሊድስ ዩናይትድ ዌስትሃም ዩናይትድን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!