ቢዝነስ

የአርሶ አደሩ በኩታገጠም የማልማት ባህል እያደገ ነው

By Abiy Getahun

October 25, 2025

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 15፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ማንደፍሮ ንጉሴ (ዶ/ር) የአርሶ አደሩ በኩታገጠም የማልማት ባህል እያደገ መጥቷል አሉ።

ዋና ዳይሬክተሩ ከፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ ግብርናውን የዘመነ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ለማድረግ አዳዲስ አሰራሮች እየተዘረጉ ነው ብለዋል፡፡

አርሶ አደሩ በኩታገጠም ሲያለማ የበለጠ ውጤታማ እየሆነ ነው ሲሉም አስረድተዋል፡፡

ከዚህ ቀደም ከግማሽ ሚሊየን ሄክታር የማይበልጥ መሬት በኩታገጠም ይለማ እንደነበር አስታውሰው፤ ኢንስቲትዩቱ ትኩረት ሰጥቶ በሰራው ስራ በአሁኑ ወቅት በኩታገጠም የሚለማው መሬት 12 ነጥብ 3 ሚሊየን ሄክታር ደርሷል ነው ያሉት።

ግብርናው በቴክኖሎጂ የታገዘ እንዲሆን በኩታገጠም የሚያለሙ አርሶአደሮች ወደ አግሪ ቢዝነስ ኩባንያ እንዲያድጉ በዕቅድ እየተሰራ መሆኑንም አብራርተዋል፡፡

መካናይዜሽንን በማስፋፋት፣ በሶላር ኢነርጂ መስራት የሚያስችል የመስኖ ልማትን ተግባራዊ በማድረግ አርሶ አደሩ በዓለም አቀፍ ደረጃ በምርት ጥራት፣ ብዛትና በዋጋ ተወዳዳሪ እንዲሆን እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

በዙፋን ካሳሁን

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡- YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.) Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook WMCC TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!