የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮጵያ ባላት ታሪክና መብት የባሕር በር የማግኘት ጥያቄዋ የሕልውና ጉዳይ ነው – ቫይስ አድሚራል ክንዱ ገዙ

By Melaku Gedif

October 25, 2025

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 15፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ባሕር ሃይል የሚሰጠውን ግዳጅ ለመወጣት የሚያስችል ሁለንተናዊ ቁመና ላይ ይገኛል አሉ የኢትዮጵያ ባሕር ሃይል አዛዥ ቫይስ አድሚራል ክንዱ ገዙ፡፡

118ኛው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ቀን “የማትደፈር ሀገር የማይበገር ሠራዊት” በሚል መሪ ሃሳብ በባሕር ኃይል ማሰልጠኛ ት/ቤት ተከብሯል፡፡

ቫይስ አድሚራል ክንዱ ገዙ በዚህ ወቅት እንዳሉት ÷ መንግስት የባሕር በር አስፈላጊነት ላይ ባለው የጸና አቋምና የመከላከያ ሠራዊቱ አመራሮች ባደረጉት ድጋፍ አንጋፋውን የኢትዮጵያ ባሕር ሃይል ወደ ቀደመ ገናና ስሙ ለመመለስ የተከናወኑ ሥራዎች ውጤታማ ናቸው።

ኢትዮጵያ በየዘመናቱ የገጠሟትን ፈተናዎች በድል እየተወጣች የመጣች ታሪካዊ ሀገር መሆኗን አውስተው ÷ የባሕር በር ጥያቄው የኢትዮጵያ የሕልውና ጉዳይ መሆኑን አስረድተዋል።

ባሕር ሃይሉ ራሱን ብቃት ባላቸው ባለሙያዎች በማደራጀት እና የተቋማት ግንባታውን ከማሳደግ ባለፈ የመነሻ ውጊያ ትጥቆች ማሟላቱን ተናግረዋል።

የባሕር በርና ባሕር ሃይል የማይነጣጠሉ መሆናቸውን ገልጸው ÷ ኢትዮጵያ ባላት ታሪክና መብት የባሕር በር የማግኘት ጥያቄ የሕልውና ጉዳይ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

ሀገራችን የባሕር በር ለማግኘት የምታደርገውን ፍትሃዊ ጥያቄ ለጋራ ተጠቃሚነት በሰጥቶ መቀበል መርሕ መስራት እንደሚገባ ማስገንዘባቸውንም የመከላከያ ኦንላይን ሚዲያ ለፋና ዲጂታል ገልጿል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!