የሀገር ውስጥ ዜና

ልዩነቶችን በውይይት የመፍታት ባህል ይበልጥ ሊዳብር ይገባል – አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ

By Melaku Gedif

October 25, 2025

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 15፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) አለመግባባቶችን በውይይት የመፍታት ባህል ይበልጥ ሊዳብር ይገባል አሉ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ፡፡

አፈ ጉባዔ ታገሰ ÷ በኢትዮጵያ ሕዝብ ትብብር እውን የሆነውን የሕዳሴ ግድብ መመረቅ የኢትዮጵያ የማንሠራራት ዘመን ጅማሮ ማሳያ ነው ብለዋል፡፡

በተጨማሪም የጋዝ ፋብሪካ እና የማዳበሪያ ፋብሪካ ለመገንባት ሥራዎች መጀመራቸውን ነው የተናገሩት፡፡

ኢትዮጵያ ትልቅ ተስፋ ያላት ሀገር መሆኗን አውስተው ÷ ይህንን በአጭር ጊዜ እውን ለማድረግም እጅ ለእጅ ተያይዞ መስራት ይገባል ነው ያሉት፡፡

አሁን ላይ እየታየ ያለውን የሥራ መንፈስ ማጠናከር አስፈላጊው ነው ያሉት አፈ ጉባዔው ÷ በዚህም የኢትዮጵያን ብልጽግና እውን ማድረግ እንደሚቻል አመልክተዋል፡፡

በግብርና ዘርፍ በስንዴ እንዲሁም በሩዝ ምርታማነት ላይ የተከናወኑ ሥራዎች ከፍተኛ ውጤት እየተመዘገበባቸው መሆኑን ተናግረዋል።

በሌማት ትሩፋት መርሐ ግብር በእንቁላል፣ በማር፣ በስጋ እና በዓሳ ሃብት ምርት ላይ የተገኙ ውጤቶች አበረታች እንደሆኑ አመልክተዋል፡፡

በአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር የተራቆቱ መሬቶች እንዲያገግሙ ከማድረግ ባለፈ በአግሮ ፕሮሰሲንግ በማስተሳሰር ከዚህ ቀደም ያልታዩ ውጤቶች መገኘታቸውን አንስተዋል፡፡

አለመግባባቶችን በመነጋገር መፍታት እንደሚገባ አመልክተው ÷ ለዚህም ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ተቋቁሞ እየተሰራ መሆኑን አስታውሰዋል።

በመነጋገርና በመመካከር ለመጭው ትውልድ የተሻለች ሀገር ማስተላለፍ እንደሚቻል ማስገንዘባቸውንም ኢዜአ ዘግቧል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!