አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 16፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአዋሽ ፈንታሌ አካባቢ ዛሬ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል አለ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦፊዚክስ፣ ሕዋ ሳይንስና አስትሮኖሚ ኢንስቲትዩት።
በዩኒቨርሲቲው የሶሲሞሎጂ ትምህርት ክፍል ኃላፊ አታላይ አየለ (ፕ/ር)፥ በአዋሽ ፈንታሌ አካባቢ በሬክተር ስኬል 4 ነጥብ 8 የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን ለፋና ዲጂታል አረጋግጠዋል።
የመሬት መንቀጥቀጡ ከጠዋቱ 2 ሰዓት ከ24 ደቂቃ አካባቢ መከሰቱን ገልጸዋል።
የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረትም አዲስ አበባ ከተማን ጨምሮ የተለያዩ አካባቢዎች ድረስ መሰማቱን ነው የገለጹት።
በአድማሱ አራጋው
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!