ስፓርት

ዛሬ አርሰናል ከክሪስታል ፓላስ እና አስቶን ቪላ ከማንቼስተር ሲቲ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል

By Adimasu Aragawu

October 26, 2025

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 16፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ዛሬ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አርሰናል ከክሪስታል ፓላስ እንዲሁም አስቶን ቪላ ከማንቼስተር ሲቲ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል።

በ9ኛው ሳምንት የሊጉ መርሐ ግብር በዛሬው ዕለት አምስት ጨዋታዎች ይደረጋሉ።

በዚህም አመሻሽ 11 ሰዓት ላይ የሊጉ መሪ አርሰናል ክሪስታል ፓላስን የሚገጥምበት ጨዋታ ይጠበቃል።

በውድድር ዓመቱ አርሰናልን የተቀላቀለው ኤበሪቼ ኤዜ የቀድሞ ቡድኑን በሚገጥምበት በዚህ ጨዋታ መድፈኞቹ የሉጉን መሪነት ለማስቀጠል ሲገቡ÷ በተለይም ካለፈው ዓመት ጀምሮ ድንቅ ብቃት እያሳየ ከሚገኘው ክሪስታል ፓላስ ከባድ ፈተና ይጠብቀዋል።

በተመሳሳይ ሰዓት አስቶን ቪላ ከማንቼስተር ሲቲ ጨዋታቸውን የሚያደርግ ሲሆን÷ ከአርሰናል በ3 ነጥብ ዝቅ ብሎ 3ኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ሲቲ ጨዋታውን በማሸነፍ የነጥብ ልዩነቱን ለማጥበብ ወደ ሜዳ ይገባል።

በተጨማሪም ወልቭስ ከበርንሌይ እና በርንማውዝ ከኖቲንግሃም ፎረስት ጋር ጨዋታቸውን በተመሳሳይ ሰዓት ሲያደርጉ÷ ምሽት 1 ሰዓት ከ30 ላይ ኤቨርተን ከቶተንሀም ጋር ይጫወታል።

ትናንት በተደረጉ የሊጉ ጨዋታዎቸ ቼልሲ እና ሊቨርፑል በተጋጣሚዎቻቸው ሲሸነፉ ማንቼስተር ዩናይትድ ማሸነፋ ይታወሳል።

በዮናስ ጌትነት

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!