የሀገር ውስጥ ዜና

11ኛው የጣና ፎረም ተጠናቀቀ

By Mikias Ayele

October 26, 2025

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 16፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በባህርዳር እና አዲስ አበባ ከተሞች “አፍሪካ በተለዋዋጩ ሉላዊ ሥርዓት” በሚል መሪ ሀሳብ ሲካሄድ የቆየው 11ኛው የጣና ፎረም ተጠናቅቋል፡፡

በፎረሙ አፍሪካን በዓለም ሥርዓት ውስጥ ተጠቃሚ ማድረግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ የተለያዩ ሀሳቦች ቀርበው የፓናል ውይይት ተደርጎባቸዋል።

የተለያዩ ሀገራት የቀድሞ መሪዎች፣ ሚኒስትሮች እና የዘርፉ ምሁራንም በውይይት መድረኮቹ ላይ ተሞክሮዎችን አካፍለዋል።

ፎረሙ በአፍሪካ ሰላምና ደህንነት ላይ በማተኮር በባህርዳር እና አዲስ አበባ ላለፉት ሶስት ቀናት ሲካሄድ ቆይቶ በዛሬው ዕለት ተጠናቅቋል።

በመዝጊያ ስነ ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የማላዊ የቀድሞ ፕሬዚዳንት እና የጣና ፎረም ቦርድ አባል ጆይስ ባንዳ (ዶ/ር)÷ አፍሪካውያን መሰል የትብብር መድረኮችን ማስፋት እንደሚገባቸው አንስተዋል።

11ሻው የጣና ፎረም በስኬት እንዲካሄድ አስተዋጽኦ ላደረጉ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።

በአሸናፊ ሽብሩ