የሀገር ውስጥ ዜና

በሁሉም ዘርፎች የሕዝብን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ የሚያስችሉ ሥራዎች ተከናውነዋል – ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)

By Adimasu Aragawu

October 27, 2025

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል በተያዘው በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ በሁሉም ዘርፎች የሕዝብን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ የሚያስችሉ ሥራዎች ተከናውነዋል አሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)።

የክልሉ የሩብ ዓመት የመንግስት እና ፓርቲ ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በወቅቱ እንዳሉት÷ በሩብ ዓመቱ ከዕቅድ አኳያ በተለይም በትምህርት፣ ጤና እና በሌሎች ማህበራዊ ዘርፎች አበረታች ውጤቶች ተመዝግበዋል።

በግብርና ዘርፍ በመኸር እርሻ ልማት የማሳ ሽፋን ማሳደግ፣ በሌማት ትሩፋት፣ የሻይ ልማት ሥራዎችን ለማስፋት የችግኝ ዝግጅትና ተከላ መከናወኑን አስረድተዋል።

ከሕዝብ የሚነሱ የመሠረተ ልማት ጥያቄዎችን መመለስ እንዲቻል የተከናወኑ ጅምር ሥራዎች እንዳሉም ጠቁመዋል።

አገልግሎት አሰጣጥን ማሳለጥ የሚያስችል መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ወደ ሥራ ለማስገባት የህንጻ ግንባታ መገባደዱን ጠቅሰው÷ በቅርቡ ለአገልግሎት ክፍት ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን አንስተዋል።

ዘላቂ ሠላምን ለማረጋገጥ የስጋት ልየታ በማድረግ በየደረጃው አስፈላጊ የፀጥታ ሥራዎች በሰፊው እየተከናወነ ይገኛልም ነው ያሉት።

በሩብ ዓመቱ በጥንካሬ የታዩ አፈጻጸሞችን በማጎልበትና መሻሻል ያለባቸው ጉዳዮችን በመለየት በትኩረት እንደሚሰራ መግለጻቸውን የክልሉ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ የሺዋስ ዓለሙ ለፋና ዲጂታል ገልጸዋል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!