አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ የውሃ ሃብት ጥበቃና አጠቃቀምን በተመለከተ ትርጉም ያላቸውን ስራዎች እየሰራች ነው አሉ የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ሃብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር)።
ሚኒስትሩ ይህንን ያሉት በ2ኛው የውሃ እና ኢነርጂ ሳምንት ማስጀመሪያ መርሐ ግብር ላይ ነው።
ኢትዮጵያ የውሃ ሃብት ጥበቃ ላይ የምትሰራው ስራና የኃይል ልማት ተግባራት ለሌሎች ትምህርት ሊሰጥ የሚችል እንደሆነም ሃብታሙ (ዶ/ር) ተናግረዋል።
ለአምስት ቀናት በአዲስ አበባ በሚካሄደው የውሃ እና ኢነርጂ ሳምንት ዐውደ ርዕይና ፓናል ውይይቶች እንደሚደረጉ ተገልጿል።
በፓናል ውይይቱ የውሃ ሃብት አጠቃቃም እና አስተዳደር የተመለከተ እንዲሁም ድንበር ተሻጋሪ ወንዞች አጠቃቀም ላይ ያሉ ልምዶችን የተመለከቱ ጉዳዮች ይዳሰሳሉ።
በለይኩን ዓለም
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!