ስፓርት

አትሌት ትዕግስት አሰፋ እና ዮሚፍ ቀጀልቻ የዓመቱ ምርጥ አትሌት ዕጩ ውስጥ ተካተቱ

By Melaku Gedif

October 27, 2025

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) አትሌት ትዕግስት አሰፋ እና አትሌት ዮሚፍ ቀጀልቻ ከስታዲየም ውጭ የዓመቱ ምርጥ የጎዳና ላይ ውድድር አትሌት ዕጩ ውስጥ ተካተቱ።

የዓለም አትሌቲክስ በዛሬው ዕለት ይፋ ባደረገው መረጃ፤ አትሌቶቹ በውድድር ዓመቱ በተለያዩ የጎዳና ላይ ውድድሮች ባስመዘገቡት ውጤት ነው ለዕጩነት መካተት የቻሉት።

በሴቶች አትሌት ትዕግስት አሰፋ፣ ሲፈን ሀሰን፣ ማሪያ ፔሬዝ፣ አንገስ ንጌቲች እና ፔሬስ ጄፕቺርቺር በእጩነት ተመርጠዋል።

በወንዶች ደግሞ አትሌት ዮሚፍ ቀጀልቻ፣ ካዮ ቦንፊም፣ ኢቫን ዱንፊ፣ አልፎንስ ሲምቡ እና ሰባስቲያን ሳዌ ከስታዲየም ውጭ የዓመቱ ምርጥ የጎዳና ላይ ውድድር አትሌት ዕጩ ሆነው መመረጣቸውን የዓለም አትሌቲክስ ይፋ አድርጓል።