አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በነዳጅ ኩባንያዎች አቅርቦትና ሥርጭት ላይ አዲስ የገበያ ድርሻ አሰራር ተግባራዊ ተደርጓል አለ የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን።
የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ደስታው መኳንንት (ዶ/ር) እንዳሉት ÷ የነዳጅ ሥርጭትን ፍትሃዊ እና ለሀገር ልማት በሚውልበት አግባብ መጠቀም ይገባል፡፡
የነዳጅ አከፋፋይ ኩባንያዎች የሚያሰራጩት ነዳጅ ለሕብረተሰቡ ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ተደራሽ እንዲሆን በጥናት ላይ የተመሰረተ የገበያ ድርሻ ቀመርና የአሰራር ሥርዓት ተግባራዊ መደረጉን ጠቅሰዋል፡፡
ከዚህ በፊት ኩባንያዎች ከነዳጅ አቅራቢ ድርጅቶች ተረክበው ለማደያዎች የሚያደርሱበት አሰራር ለሕገ ወጥነት በር የከፈተ እንደሆነ በጥናት መለየቱን ተናግረዋል።
በጥናቱ መሠረትም በቀጥታ ተጠቃሚ የሆኑ ቁልፍ የልማት ሴክተሮች በሚጠይቁበት ቀን በቀጥታ እንዲደርሳቸው እና ለኮንትሮባንድ ተጋላጭ ለሆኑ አካባቢዎች ደግሞ በኮታ እንዲቀርብላቸው እንደሚደረግ አብራርተዋል።
የተከለሰው የገበያ ድርሻ ቀመር የነዳጅ አቅርቦትን ከማሻሻል ጎን ለጎን ፍትሃዊ ተደራሽነትን ባረጋገጠ መንገድ ምርቱን በቁጠባና ውጤታማነት መርሕ መጠቀም ያስችላል ነው ያሉት።
እንዲሁም ከጂቡቲ ጀምሮ የነዳጅ ሥርጭቱን ለመከታተል የሚያስችል አሰራር ተግባራዊ እንደሚደረግ ገልጸው÷ ይህም በነዳጅ ሥርጭት እና ተደራሸነት ብሎም ፍትሃዊነት ላይ ጉልህ ለውጥ ያመጣል ብለዋል፡፡
ቀደም ሲል ለነዳጅ አከፋፋይ ኩባንያዎች የነዳጅ አቅርቦት ድርሻ የተለያዩ መስፈርቶችን መነሻ በማድረግ ሲሰራ ነበር ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ÷ በነዳጅ ግብይት ላይ የጎላ ጥፋት በተገኘባቸው አካላት ላይ ሕጋዊ ርምጃዎች መወሰዳቸውን አስታውሰዋል።
በየሻምበል ምህረት
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!