የሀገር ውስጥ ዜና

የካሉብ ጋዝ ፕሮጀክት ሀገር ወዳድነት በግልፅ የታየበት ስራ ነው

By Abiy Getahun

October 27, 2025

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የካሉብ ጋዝ ፕሮጀክት ሀገር ወዳድነት በግልፅ የታየበት ስራ ነው አሉ የፀጥታ ጥምር ኮሚቴው ሰብሳቢና በቀጠናው የተሰማራው ክፍለ ጦር አዛዥ ኮሎኔል ልጅዓለም ምትኩ፡፡

አሁን ላይ ተጠናቆ በከፊል ስራ የጀመረው የካሉብ የተፈጥሮ ጋዝ ፕሮጀክት በሰላም እንዲጠናቀቅ የመከላከያ ሠራዊት እና ሌሎች የፀጥታ ሀይሎች በንቃት በመጠበቅ ለውጤት እንዲበቃ ማድረጋቸው ተመላክቷል፡፡

የሕይወት መስዋዕትነት የተከፈለበት እና ሀገር ወዳድነትን በግልፅ ያሳየ ሥራ ስለመሆኑ ኮሎኔል ልጅዓለም ምትኩ አስረድተዋል፡፡

የምስራቅ ምድብ ፌዴራል ፖሊስ ሬጅመንት አዛዥና የፀጥታ ጥምር ኮሚቴው ም/ሰብሳቢ ተወካይ ኮማንደር ጎይቶም ዓለም በበኩላቸው፤ በመከላከያ ሠራዊት የበላይ ሰብሳቢነት ከፌዴራል እስከ ክልል የፀጥታ አካላት ተዋቅሮ ኃላፊነቱን እየተወጣ ይገኛል ብለዋል።

በሶማሌ ክልል የቆራሂ ዞን ፖሊስ መምሪያ ም/ኮማንደር መሃመድ ኢብራሂም ለአንድ ዓላማ ተግባብተንና ተደጋግፈን በመስራት የሀገራችን ዕድገት እንዲፋጠን ሰላማዊ እንቅስቃሴ እንዲቀጥል የበኩላችንን እየተወጣን ነው ሲሉ ተናግረዋል።

የካሉብ ጋዝ ፕሮጀክት የጥበቃ ጥምር ኮሚቴ ኃላፊነቱን በሚገባ እየተወጣ እንደሚገኝ መገለፁን የመከላከያ ኦንላይን ሚዲያ ለፋና ዲጂታል ገልጿል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡- YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!