ዓለምአቀፋዊ ዜና

ሁለት የአሜሪካ ባህር ኃይል አውሮፕላኖች በደቡብ ቻይና ባህር ተከሰከሱ

By Mikias Ayele

October 27, 2025

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ሁለት የአሜሪካ ባህር ኃይል አውሮፕላኖች በ30 ደቂቃ ልዩነት በደቡብ ቻይና ባህር ላይ ወድቀው ተከስክሰዋል፡፡

አደጋው አውሮፕላኖቹ በደቡብ ቻይና ባህር ላይ መደበኛ ስራቸውን ሲያከናውኑ በነበሩበት ወቅት መከሰቱ ነው የተገለጸው።

በረራውን ሲያደርጉ የነበሩ አምስት የበረራ ሰራተኞች ከአደጋው መትረፋቸውና የተከሰከሱት አውሮፕላኖች ወደ አሜሪካ ባህር ኃይል መላካቸው ተገልጿል፡፡

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ክስተቱን “ያልተለመደ” ሲሉ በመግለጽ÷ ምን አልባትም የነዳጅ ችግር ሊሆን እንደሚችል ተናግረዋል፡፡

የአደጋው ምክንያት እየተጣራ እንደሆነና በቅርቡም ይፋ እንደሚደረግ አንስተው÷ ተደብቆ የሚቀር ነገር እንደሌለ አመላክተዋል፡፡

የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጉ ጂያኩን÷ የሁለቱን የባህር ኃይል አውሮፕላኖች አደጋን ለማጣራት የቻይና መንግሥት ምርመራ ጀምሯል ማለታቸውን ፎርስስ ኒውስ ዘግቧል፡፡

በሚኪያስ አየለ