አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) በመጀመሪያው ሩብ ዓመት የጀመረውን የሳይበር ጥቃት መከላከል አጠናክሮ ማስቀጠል እንዳለበት ተመላከተ።
በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የውጭ ግንኙነትና ሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የተቋሙን የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድና የመጀመሪያውን ሩብ አፈጻጻም ሪፖርት አዳምጧል።
የቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ ፈትሂ ማህዲ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት÷ ኢመደአ ከተቋማት ጋር በትብብር በመሥራት ሜጋ ፕሮጀክቶችንና የፋይናንስ ተቋማትን ከሳይበር ጥቃት መከላለከል እንዳለበት አስገንዝበዋል፡፡
ኢመደአ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ትእግሥት ሃሚድ በበኩላቸው÷ በሩብ ዓመቱ በተለያዩ ተቋማት መሠረተ ልማቶች 13 ሺህ 443 የሳይበር ጥቃት ሙከራዎች መደረጋቸውን አንስተው፤ 97 ነጥብ 8 በመቶ መከላከል መቻሉን ተናግረዋል፡፡
የሳይቨር ጥቃቶችን የመከላከል አቅሙ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ መምጣቱንም አመላክተዋል።