አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በኦሮሚያ ክልል በ2018 በጀት ዓመት የቡና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ በተከናወኑ ሥራዎች ከ16 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት ይገኛል ተብሎ ይጠበቃል አለ የክልሉ ግብርና ቢሮ፡፡
የቢሮው ም/ኃላፊ መሃመድሳኒ አሚን ለፋና ዲጂታል እንደገለጹት ፥ ባለፉት ዓመታት የቡና ምርትና ምርታማነትን እንዲሁም ጥራትን በማሳደግ ረገድ አበረታች ውጤት ተገኝቷል፡፡
አዳዲስ የቡና ኢኒሼቲቮችን በማስተዋወቅ፣ ምርምሮችን በማስፋት፣ የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀምና ዘመናዊ አሰራሮችን በመተግበር በርካታ ሥራዎች ተከናውነዋል ብለዋል፡፡
በዚህም በክልሉ የቡና ምርት በእጥፍ የጨመረ ሲሆን ፥ በ2011 ዓ.ም በሄክታር ይገኝ ከነበረው 6 ኩንታል ምርት አሁን ላይ ወደ 9 ኩንታል ከፍ ማድረግ መቻሉን አመልክተዋል፡፡
በበጀት ዓመቱ ከ16 ሚሊየን ኩንታል በላይ ቡና ይመረታል ተብሎ እንደሚጠበቅ ጠቅሰው ፥ በምርት አሰባሰብ ሒደት የአርሶ አደሩን ግንዛቤ በማሳደግ ጥራቱን የጠበቀ ቡና ለገበያ ለማቅረብ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
የዘርፉን ምርትና ምርታማነት ከማሳደግ ባሻገር ለጥራት ትኩረት በመስጠት በተሰሩ ሥራዎች በክልሉ ተመርቶ ለውጭ ገበያ የሚቀርበው ቡና መጠን በከፍተኛ ደረጃ መጨመሩን ተናግረዋል፡፡
ለአብነትም በ2017 በጀት ዓመት በክልሉ ተመርቶ ለማዕከላዊ ገበያ ከቀረበው ከ500 ሺህ ቶን በላይ የቡና ምርት ውስጥ 400 ሺህ ቶን ያህሉ ወደ ውጭ ተልኳል ነው ያሉት፡፡
በኃይለማርያም ተገኝ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!