የሀገር ውስጥ ዜና

መንግስት የዋጋ ንረቱን ለማረጋጋት 440 ቢሊየን ብር ድጎማ አድርጓል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

By Hailemaryam Tegegn

October 28, 2025

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) መንግስት የዋጋ ንረቱን ለማረጋጋት 440 ቢሊየን ብር ድጎማ አድርጓል አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በ6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ በሰጡት ማብራሪያ የዚህ ወር የዋጋ ንረት ወደ 11 ነጥብ 7 በመቶ ዝቅ እንዲል ማድረግ መቻሉን ጠቁመዋል፡፡

ይህም ከለውጡ ወዲህ የተመዘገበ ዝቅተኛ የዋጋ ንረት መጠን መሆኑን ጠቅሰው፥ መንግስት የዋጋ ንረቱን ለማረጋጋት 440 ቢሊየን ብር ድጎማ አድርጓል ብለዋል፡፡

ከዚህም ውስጥ በድጎማ ለሴፍቲኔት 60 ቢሊየን ብር፣ ለአፈር ማዳበሪያ 84 ቢሊየን ብር፣ለነዳጅ 140 ቢሊየን ብር እንዲሁም ለመንግስት ሰራተኞች ደሞዝ ጭማሪ 160 ቢሊየን ብር ድጎማ ተደርጓል፡፡

የተማሪዎች ምገባ፣ የማእድ ማጋራት እንዲሁም የመንግስት የገንዘብ ፖሊሲ ለኑሮ ውድነቱ መቀነስ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አድርገዋል ነው ያሉት፡፡