አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያን አቅም ላኪው ያውቀዋል ተላላኪው ግን ይጓጓል አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን ያሉት በ6ኛ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ስብሰባ ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሳላቸው ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽና ማብራሪያ ነው።
በኢትዮጵያ ውስጥ ለረጅም ጊዜ የቆየው እርስ በርስ መጋጨት መብቃት አለበት የሚለው ትክክለኛ ሃሳብ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)÷ የኢትዮጵያን እድገትና ሰላም የማይፈልጉ ሀገራት በጦርነት ማሸነፍ እንደማይችሉ ያውቁታል ብለዋል።
ኢትዮጵያ ደካማ ሆና በሁለት እግሯ መቆም እንዳትችል የሚሰሩ ሀገራት ባሉበት ሁኔታ ኢትዮጵያውያን የሀገራዊ ጥቅምን ለይተው ማወቅ ካልቻሉ፣ ለፖለቲካ ፍጆታ፣ ለጠላት ፍላጎት ተላልፈው ከተሰጡ የተሟላ ሰላም ማምጣት ያስቸግራልም ነው ያሉት፡፡
በተነገረው ቁጥር ዘሎ እዚህ የሚመጣ ስለሚመስለው ተላላኪ ይጓጓል፤ እየተላከ እንደሆነ እና በራሱ ዓላማ እንዳልቆመ እንዲሁም ራሱ የያዘውን ሃሳብ ይዞ ቢመጣ ለውጥ እንደማያመጣ ያውቃል ግን ጉጉት ይይዘዋል ሲሉም አብራርተዋል።
ኢትዮጵያ ውስጥ የሆነን ሰፈር እገነጥላለሁ እጠቀልላለሁ የሚል ገቢር ነበብ አይደለም ኢትዮጵያ ለመገንጠልም ለመጠቅለልም አመቺ አይደለችም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ÷ ይህን ባለማወቅ በጉጉትና በመሻት የሚጋለቡ ፈረሶች የእነሱን ፍላጎት ለማሳካት ቀላል መንገድ የሚመስላቸው ከጠላት ጋር ማበር ነው ብለዋል።
ብዙዎቹን ስንመለከት መገንጠልም መጠቅለልም ሲባል ሰምተው ነው እንኳን ለመጠቅለል አክብሮ ለመኖርም ጊዜው ከባድ እንደሆነ አልተረዱትም፤ ይህ ችግር ባለበት የተሟላ ሰላም ማምጣት ውጣ ውረድ አለው ሲሉም አመላክተዋል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!