አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ማንም በጉልበት እኛን ማስገደድ አይችልም አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በ6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ በሰጡት ማብራሪያ÷ ሁሉም ሀገር ሃብቱ ይብዛም ይነስ የተፈጥሮ ጸጋውን ሌላውን በማይጎዳ መልኩ የመጠቀም መብት አለው ብለዋል።
ሀገራት ብሄራዊ መብቶች እና ስጋቶች እንዳላቸው ገልጸው÷ ይህም የሚወሰነው ባለው እውቀትና መረጃ መሆኑን አመላክተዋል።
ኢትዮጵያ ኢፍትሃዊ እና የመጨረሻው በደል የተፈጸመባት ሀገር ናት በማለት ገልጸው÷ ዓባይን ኢትዮጵያ ተጠቀመች እንጂ ማንን መች ጎዳች፤ ኃይል አመረትን እንጂ መች ውሃ ከለከልን? ሲሉም በምሳሌነት አንስተዋል።
ኢትዮጵያ ማንንም የመጉዳት ፍላጎት የላትም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ÷ ውሃውን ሳንጠቀም ስጋቱ ድርቅ ነበር፤ አሁንስ ስጋቱ ጎርፍ ሆነ ባንገድብ ኖሮ ጎርፉ ምን ይሆን ነበር ሲሉም ጠይቀዋል።
የመላው ኢትዮጵያውን ፍላጎት በጋራ መስራት እና ማምረት ነው፤ ከራሳችን አልፈን ለመላው አፍሪካ መትረፍ እንችላለን ብለዋል።
ከግብጽ ጋር በስምምነትና በድርድር መግባባት እንፈልጋለን ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)÷ ማንም ሰው በጉልበት እኛን ማስገደድ አይችልም፤ ኢትዮጵያውያን ለዚህ አልተሰራንም፤ የሚያዋጣው መግባባት እና መስማማት ነው ሲሉም አጽንዖት ሰጥተዋል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!