አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የመንግሥት አግልግሎት አሰጣጥን ከብልሹ አሰራር የማጽዳት ተግባር ተጠናክሮ ይቀጥላል አሉ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)።
ርዕሰ መስተዳድሩ የሚዛን አማን መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን በዛሬው ዕለት መርቀው ሥራ አስጀምረዋል።
ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ከዲጂታሉ ዓለም ጋር በመራመድ ቀልጣፋ አገልግሎትን ለመስጠት የሚያስችል ነው።
ማዕከሉ ዲጂታል ኢኮኖሚን ለማሳለጥ የጎላ ፋይዳ እንዳለው ገልጸው÷ በሌሎች አምስት የክልሉ ከተሞች ተጨማሪ ማዕከላት ይገነባሉ ብለዋል።
ከ350 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎቱ÷ 32 አገልግሎቶችን መስጠት እንደሚችልና በቀጣይ 50 ለማድረስ እንደሚሰራ ተገልጿል። የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ወ/ሮ አልማዝ መሰለ በበኩላቸው÷ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ዜጎች ከመንግሥት የሚፈልጓቸውን አገልግሎቶች በአንድ ቦታ እንዲያገኙ እንደሚያስችል ተናግረዋል። በሀገር አቀፍ ደረጃ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫዎች 18 መድረሳቸውን አንስተው÷ በክልሉ ሌሎች ማዕከላት ተከፍተው ዜጎች የመንግስትን አገልግሎት በክብር እንዲያገኙ ኮሚሽኑ ድጋፉን አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል። በፍሬው አለማየሁ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!