ቢዝነስ

የእንስሳት ልማትና የእንስሳት ተዋጽዖ ላይ ያተኮረ አውደ ርዕይ ተከፈተ

By Melaku Gedif

October 30, 2025

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ከ5 ሺህ በላይ የምስራቅ አፍሪካና ዓለም አቀፍ ሀገራት ጎብኚዎች የሚሳተፉበት የእንስሳት ልማትና የእንስሳት ተዋጽዖ ላይ ያተኮረ አውደ ርዕይ በሚሊኒየም አደራሽ ተከፍቷል።

ከዛሬ ጀምሮ ለሶስት ተከታታይ ቀናት በሚካሄደው አውደ ርዕይና ጉባኤ ከ14 ሀገራት የተወጣጡ ከ100 በላይ የእንስሳት ሃብት ዘርፍ ተዋናዮች፣ የሀገራት አምባሳደሮችና የዘርፉ ባለሙያዎችም ይሳተፉበታል።

ሁሉን አቀፍ የእንስሳት እርባታ ቴክኖሎጂ፣ ግብዓትና መፍትሄዎች ላይ ትኩረት የሚያደርገው አውደ ርዕይ፤ የእንስሳት ሀብት የገበያ ሰንሰለቶችን እና የኢንቨስትመንት እድሎች ለማስተዋወቅም የሚያግዝ ነው ተብሏል።

በተጨማሪም በዘርፉ ውጤታማ ከሆኑ ሀገራት ልምድ ለመለዋወጥና ተሞክሯቸውን ለመቅስም እንደሚያግዝ ተመላክቷል።

መንግስት በሰጠው ትኩረትና በሌማት ትሩፋት ኢኒሼቲቭ የአራት ዓመት ፕሮግራም የወተት፣ የእንቁላል፣ የዶሮ ስጋ እና የማር ምርቶችን በከፍተኛ ደረጃ ለማሳደግ ግብ አስቀምጦ እየተንቀሳቀሰ እንደሆነ ተጠቁሟል።

በታምራት ደለሊ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!