ስፓርት

ኢትዮ ኤሌክትሪክ ኢትዮጵያ ቡናን አሸነፈ

By Adimasu Aragawu

November 02, 2025

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 23፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ4ኛ ሳምንት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ኢትዮጵያ ቡናን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

የኢትዮ ኤሌክትሪክን ማሸነፊያ ግብ ከእረፍት መልስ ሀብታሙ ሸዋለም በ48ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥሯል።

ኢትዮ ኤሌክትሪክ በጨዋታው ማሸነፉን ተከትሎ 10 ነጥብ በመሰብሰብ ሊጉን በበላይነት መምራት ጀምሯል።

በሌላ በኩል የውድድር ዓመቱን ሁለተኛ ሽንፈት ያስተናገደው ኢትዮጵያ ቡና በአራት ነጥቦች 10ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

የሊጉ መርሐ ግብር ሲቀጥል ቀን 9 ሰዓት ላይ ሲዳማ ቡና እና ወላይታ ድቻ ሲጫወቱ፣ ነገሌ አርሲ ከባህር ዳር ከተማ ቀን 10 ሰዓት እንዲሁም 12 ሰዓት ላይ ፋሲል ከነማ እና ምድረ ገነት ሽረ ይገናኛሉ።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!