አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በሀገር መከላከያ ሰራዊት ሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት የተፈፀመበት 5ኛ ዓመት እየታሰበ ይገኛል።
ቀኑ በቢሾፍቱ አየር ወለድ ማሰልጠኛ ማዕከል “እንዳይደገም፤ መቼም አንረሳውም” በሚል መሪ ሐሳብ ነው እየታሰበ የሚገኘው።
በመርሐ ግብሩ ከአምስት ዓመታት በፊት የተፈፀመውን ጥቃት የሚያስታውሱ የተለያዩ ዝግጅቶች እየተከናወኑ ነው።
በሥነ ሥርዓቱ ላይ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፣ የጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀነራል አበባው ታደሰ እንዲሁም ጀነራል መኮንኖች፣ የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተሳትፈዋል።
በአንዷለም ተስፋዬ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!