አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ4ኛ ሳምንት ሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ሀዋሳ ከተማ እና ሸገር ከተማ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፈዋል።
ቀን 10 ሰዓት ላይ አዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ሸገር ከተማ ቅዱስ ጊዮርጊስን 1 ለ 0 አሸንፏል።
ያሬድ መኮንን በ46ኛው ደቂቃ ላይ ባስቆጠራት ግብ ነው ሸገር ከተማ ሦስት ነጥብ ይዞ መውጣት የቻለው፡፡
በተመሳሳይ ሰዓት በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደ ጨዋታ ሀዋሳ ከተማ መቐለ 70 እንደርታን 3 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል።
የሀዋሳ ከተማን ማሸነፊያ ግቦች ጌታነህ ከበደ (2) እና ያሬድ ብሩክ ሲያስቆጥሩ÷ የመቐለ 70 እንደርታን ብቸኛ ግብ ደግሞ ሱሌማን ሀሚድ ከመረብ አሳርፏል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!