የሀገር ውስጥ ዜና

ጥቅምት 24 ሲታወስ ሀገራዊ ህልውናን በማረጋገጥ ታሪክ የሰሩ ጀግኖችን በማሰብ መሆን አለበት – ሌ/ጄ ዘውዱ በላይ

By Melaku Gedif

November 03, 2025

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጥቅምት 24 ሲታወስ ህግ በማስከበርና ሀገራዊ ህልውናን በማረጋገጥ ታሪክ የሰሩ ጀግኖችን በማሰብ መሆን አለበት አሉ የዳሎል ማዕከላዊ ዕዝ አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ዘውዱ በላይ።

በሀገር መከላከያ ሠራዊት ሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት የተፈፀመበት 5ኛ ዓመት “እንዳይደገም ፤ መቼም አንረሳውም” በሚል መሪ ሃሳብ የማዕከላዊ ዕዝ አመራሮች፣ አባላት እና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በተገኙበት በፓናል ውይይት በጅማ ከተማ ታስቧል።

በመድረኩ ላይ የሠራዊቱ አባላት፤ ሠራዊቱ ላይ የተፈጸመው ጥቃት ብዙ ምስቅልቅል ማስከተሉን አስታውሰው፤ የሰላምን ዋጋ መገንዘብ ይገባል ብለዋል።

ሠራዊቱ ላይ የደረሰው በደል እንዳይደገም በትጋት መስራት እንደሚያስፈልግም አስገንዝበዋል።

የዕዙ አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ዘውዱ በላይ በበኩላቸው፤ ቀኑ ሲታሰብ በወቅቱ የተፈጠረውን ሁኔታ በመኮነን፣ በክህደት ከጀርባቸው ተወግተው መስዋዕት የሆኑ የሠራዊት አባላትን በማስታወስ መሆን አለበት ብለዋል።

ህግ በማስከበርና የሀገር ህልውናን በማረጋገጥ ታሪክ የሰሩ የሰራዊት አባላትን ጀግንነት በማውሳት መሆን እንዳለበትም አስገንዝበዋል።

የኢትዮጵያ ህዝብ ጥቃቱን ለመቀልበስ ያሣየው አለኝታነት የሚደነቅ መሆኑን ጠቅሰው፤ ምስጋና አቅርበዋል።

በአቤንኤዘር ታየ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡- YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!