አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የትግራይ ክልል ሕዝብ ሕወሓት በሰሜን ዕዝ ላይ በፈጸመው ጥቃት አዝኗል አሉ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ።
በሀገር መከላከያ ሠራዊት ሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት የተፈፀመበት 5ኛ ዓመት “እንዳይደገም ፤ መቼም አንረሳውም” በሚል መሪ ሃሳብ በዛሬው ዕለት ታስቦ ውሏል።
ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በመርሐ ግብሩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት÷ ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም ሕወሓት በሰሜን ዕዝ ላይ በፈፀመው ጥቃት የክልሉ ሕዝብ አዝኗል ነው ያሉት።
የመከላከያ ሰራዊት በሕግ ማስከበሩ ወቅት የትግራይ ሕዝብ ትንኮስ አለማድረጉንና በሰሜን ዕዝ ላይ የተፈፀመውን ክህደትም እንደማይቀበል አንስተዋል፡፡
በወቅቱ የደረሰው ጥቃትም መካድ የለመደ የአንድ ከሃዲ ቡድን ስራ ነው ያሉት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ÷ ይህንንም ከጀመረ 50 ዓመቱ ነው ብለዋል።
ቡድኑ በሻዕቢያ ተቀጥሮ ኢትዮጵያን የባህር በር ያሳጣ ከሀዲ ነው በማለት ገልጸው፤ ኑ እንታረቅ ብሎ ፖለቲካ ድርጅትን በእርቅ መድረክ ያረደና ሰሜን ዕዝ ላይም ይህንን የደገመ ከሃዲ ቡድን ነው ሲሉ አብራርተዋል።
አሁንም በየቀኑ እየካደ ያለና በኢትዮጵያ ውስጥ የተፈጠረ የክህደት ኃይል እንደሆነም ጠቅሰዋል።
ይህ ኃይል እስካልተነቀለ ድረስ ኢትዮጵያ ሰላም አታገኝም ሲሉም አመልክተዋል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!