አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ኢትዮጵያ የአርበኞች ሀገር ናት፤ መከላከያ ሰራዊት የአባቶቹን አርበኝነት ነው የወረሰው አሉ።
ፊልድ ማርሻሉ ይህንን ያሉት በሀገር መከላከያ ሠራዊት ሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት የተፈፀመበት 5ኛ ዓመት “እንዳይደገም፤ መቼም አንረሳውም” በሚል መሪ ሃሳብ በታሰበበት ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት ነው።
ኢትዮጵያ የአርበኞች ሀገር ናት ስንል ገዢ ባህሪያችን ነው ያሉት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ÷ ቀላል የማይባል ባንዳ እንዳላትም ገልጸዋል።
ይህም በየዘመኑ መታየቱን ገልጸው፤ በወቅቱ የኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ስላልነበረ በደምብ እንደማይታወቅና አሁን ግን የግሎባላይዜሽን ዘመን ስለሆነ የሚደበቅ ነገር የለም ብለዋል።
በዚህም ምክንያት ሲደበቅ የነበረ ባንዳ በገሃድ መውጣቱን አመላክተው÷ የሰሜን ዕዝ ጥቃት የባንዳ ስራ ነው በማለት ገልጸዋል።
በአድማሱ አራጋው
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!