አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ፈረንሳዊው ተጫዋች ዴዝሬ ዱዌ የ2025 የጎልደን ቦይ ሽልማት አሸናፊ ሆኗል፡፡
የ20 ዓመቱ ተጫዋች በ2024/25 የውድድር ዓመት ከፒኤስጂ ጋር የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ እና የሊጉን ጨምሮ የተለያዩ ዋንጫዎችን በማንሳት ስኬታማ የውድድር ጊዜ ማሳለፉ ይታወሳል፡፡
ዱዌ በውድድር ዓቱ በፈረንሳይ ሊግ-1 እና በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ በድምሩ 11 ግቦችን ሲያስቆጥር፥ 11 ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ አቀብሏል፡፡
ሽልማቱ በአውሮፓ ታላላቅ ሊጎች የሚጫወቱ እድሜያቸው ከ21 ዓመት በታች የሆኑ ተጫዋቾችን ብቻ ተሳታፊ የሚያደርግ ነው።
የጣሊያኑ የስፖርት ጋዜጣ ቱቶ ስፖርት የሚያዘጋጀው ይህ ሽልማት ዘንድሮ 23ኛ አመቱን ይዟል።