ዓለምአቀፋዊ ዜና

የአሜሪካ የቀድሞ ምክትል ፕሬዚዳንት ዲክ ቼኒ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

By abel neway

November 04, 2025

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአሜሪካ የቀድሞ ምክትል ፕሬዚዳንት ዲክ ቼኒ በ84 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፡፡

ምክትል ፕሬዚዳንቱን ለሞት የዳረጋቸው የሳንባ ምች እና ልብ በሽታ መሆኑን ቤተሰቦቻቸው መናገራቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ጆርጅ ደብሊው ቡሽ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት በነበሩበት ወቅት በፈረንጆቹ ከ2001 እስከ 2009 ድረስ ዲክ ቼኒ አሜሪካን በምክትል ፕሬዚዳንትነት አገልግለዋል፡፡

ከ9/11 ጥቃት በኋላ አሜሪካ በሽብርተኝነት ላይ ዘመቻ ስትከፍት ቁልፍ ሚና የነበራቸው ዲክ ቼኒ፤ ሀገራቸው ኢራቅ ጅምላ ጨራሽ መሳሪያ ታጥቃለች በሚል ባካሄደችው ዘመቻም ዋና አማካሪ እንደነበሩ ይነገርላቸዋል።

ዲክ በፈረንጆቹ 1970 የፕሬዚዳንት ጄራልድ ፎርድ የኋይት ሃውስ ጸሃፊ በመሆንም አገልግለዋል፡፡

በአቤል ነዋይ