ዓለምአቀፋዊ ዜና

በአሜሪካ በጭነት አውሮፕላን መከስከስ አደጋ የ7 ሰዎች ሕይወት አለፈ

By Yonas Getnet

November 05, 2025

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 26፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአሜሪካ ኬንታኪ ግዛት ትናንት ምሽት በደረሰ የዩፒኤስ ጭነት አውሮፕላን መከስከስ አደጋ የ7 ሰዎች ሕይወት አልፏል፡፡

የጭነት አውሮፕላኑ ከሉዊስቪል ሙሐመድ አሊ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ መብረር በጀመረ ጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ መከስከሱ ተመላክቷል፡፡

የኬንታኪ ግዛት አስተዳዳሪ አንዲ በሺዬር÷ የጭነት አውሮፕላኑ ከተነሳ በኋላ ብዙም ሳይቆይ የመፈንዳት አደጋ እንዳጋጠመው አስረድተዋል፡፡

በተከሰተው አደጋም እስካሁን የ7 ሰዎች ሕይወት ያለፈ ሲሆን ÷11 ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድ ጉዳት መድረሱን አመልክተዋል፡፡

የሟቾች ቁጥር ሊያሻቅብ እንደሚችል ጠቁመው÷ የአደጋውን መንስኤ ለማወቅ ምርመራ እየተካሄደ ይገኛል ነው ያሉት፡፡

አደጋውን ተከትሎ የተፈጠረውን የእሳት አደጋ በፍጥነት መቆጣጠር መቻሉን ገልጸዋል፡፡

የበረራ ቁጥሩ 2979 የሆነው የጭነት አውሮፕላን 38 ሺህ ጋሎን ነዳጅ ጭኖ ወደ ሆኖሉሉ ሊያቀና እንደነበር ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

በዮናስ ጌትነት

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!