አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 12፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 22 ሺህ 101 የላብራቶሪ ምርመራ 1 ሺህ 386 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።
በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 32 ሺህ 722 መድረሱንም የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ባወጡት መረጃ አመላክተዋል።
ከዚህ ባለፈ የ28 ሰዎች ህይወት በቫይረሱ ምክንያት ያለፈ ሲሆን፥ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 572 መድረሱንም አመላክተዋል።
በሌላ መልኩ በትናንትናው እለት 414 ሰዎች ከኮሮና ቫይረስ ያገገሙ ሲሆን፥ በአጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 12 ሺህ 938 መድረሱም ተገልጿል።
ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ እስካሁን 651 ሺህ 311 ሰዎች ምርመራ የተደረገ ሲሆን፥ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 32 ሺህ 722 ደርሷል።
አሁን ላይ ቫይረሱ ያለባቸው ሰዎች ቁጥር 19 ሺህ 210 ሲሆን፥ ከእነዚህም 216 ሰዎች በጽኑ የታመሙ መሆናቸውንም የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።
እስካሁን በኢትዮጵያ 12 ሺህ 938 ሰዎች ከቫይረሱ ሲያገገሙ፤ የ572 ሰዎች ህይወት አልፏል፤ 2 ሰዎች ወደ ሀገራቸው መመለሳቸው ይታወሳል።
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።