የሀገር ውስጥ ዜና

የወጣቶችን ስብዕና የሚያንጸው “በጎነት ለአብሮነት” ስልጠና…

By Yonas Getnet

November 05, 2025

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 26፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ዘላቂ የሰላም ግንባታን እውን ለማድረግ ወጣቶች ላይ በትኩረት መስራት ይገባል አለ የሰላም ሚኒስቴር፡፡

በ14ኛ ዙር ‘የበጎነት ለአብሮነት’ ስልጠና የወሰዱ ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች የተወጣጡ ወጣቶች ምረቃ ሥነ ሥርዓት በጅማ ከተማ ተካሂዷል።

በሰላም ሚኒስቴር የሥራ አመራር ዋና ሥራ አስፈጻሚ መብራቱ ካሳ በዚህ ወቅት እንዳሉት ÷ የበጎነት ለአብሮነት ስልጠና የወጣቶችን መልካም ሥነ ምግባር በመገንባት በሀገር ፍቅር እንዲታነጹ ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል።

ከዚህ በፊት ከ60 ሺህ በላይ ወጣቶች ስልጠና መውሰዳቸውን ገልጸው÷ ይህም የወጣቶችን ስብዕና በመገንባት ሀገራዊ ለውጥ እንዲመዘገብ ጉልህ ሚና ተጫውቷል ብለዋል።

የሰላም ግንባታን ለማሳካት ወጣቶች ላይ በትኩረት መስራት ይገባል ያሉት አቶ መብራቱ ÷ ወጣቶች በተመደቡበት አካባቢ የሰላም አምባሳደር በመሆንና በበጎ ሥራ ተጽዕኖ መፍጠር እንደቻሉ ጠቅሰዋል።

በ14ኛው ዙር ከ5 ሺህ በላይ ሰልጣኝ ወጣቶች በጅማ፣ ሀዋሳ፣ ወሎ፣ ወልቂጤ እና ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲዎች ስልጠና መውሰዳቸው ተመልክቷል፡፡

ሰልጣኞች በቀጣይ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ተሰማርተው የተለያዩ በጎ ፈቃድ አገልግሎቶችን የሚሰጡ ይሆናል፡፡

በአቤንኤዘር ታየ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!