አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 27፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ የጀመረችውን የኒውክሌር ኃይል ልማት በትብብር በመገንባት እውን እንዲሆን እንሰራለን አሉ በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኢቭጌኒ ተርኪሂን።
አምባሳደር ኢቭጌኒ ተርኪሂን ሁለቱን ሀገራት በሚጠቅሙ ጉዳዮች ላይ በመምከር በትብብር እንሰራለን ብለዋል።
አሁን ላይ ኢትዮጵያ የጀመረችው የኒውክሌር ኃይል ልማት ፕሮጀክትን ለማሳካት ሩሲያ የተሻለ ልምድና የተማረ የሰው ኃይል ያላት መሆኗን አንስተው÷ ፕሮጀክቱ እውን እንዲሆን በትብብር እንደሚሰራ ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ተናግረዋል።
የአፍሪካ ፖለቲካዊ ጉዳዮች ተመራማሪ የሆኑት ሚፍታህ መሐመድ በበኩላቸው÷ ያደጉት ሀገራት የሚታወቁት በቴክኖሎጂያቸው እንደሆነ ገልጸው፤ ኢትዮጵያ በኒውክሌር ቴክኖሎጂ ላይ የጀመረችው እንቅስቃሴ ከግብርና ወደ ቴክኖሎጂ መር ኢኮኖሚ ለምታደርገው ሽግግር ወሳኝ ሚና እንዳለው አስረድተዋል።
የኒውክሌር ልማት ስራ ካለው የኢነርጂ አቅም፣ ኢንቨስትመንት፣ ኢንዱስትሪ እና ዕውቀት ሽግግርን ጨምሮ ዘርፈ ብዙ ጥቅሞች እንደሚያስገኝና የሀገራትን ተደማጭነት እንደሚጨምር ገልጸዋል።
ሩሲያ በኒውክሌር ዘርፍ ከፍተኛ አቅም አንዳላት አውስተው÷ በሁለቱ ሀገራት በዘርፉ ያደረጉት ስምምነት በትክክል ሊተገበር የሚችል እንደሆነ ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ማጠናቀቋ የተጀመሩ ግዙፍ ፕሮጀክቶች የኢትዮጵያን ሰርቶ የማሳየት አቅም ገላጮች መሆናቸውን አመላክተዋል።
የኒውክሌር ኃይል ከኃይድሮ ኤሌክትሪክ ኃይል ቀጥሎ በዓለም የአየር ንብረት ላይ ዝቅተኛ ተጽዕኖ በማሳደር ንጹህ የኃይል ምንጭ ነው ያሉት ደግሞ የኒውክሌር ፊዚክስ ባለሙያ ሩቂያ አሊ (ዶ/ር) ናቸው።
የኒውክሌር ቴክኖሎጂን በሰላማዊ መንገድ መጠቀም ለግብርና፣ ጤና፣ ጥናትና ምርምር እንዲሁም ለተለያዩ አገልግሎቶች ከፍተኛ አስተዋጽዖ እንዳለውም አስረድተዋል።
በዮናስ ጌትነት
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!