የሀገር ውስጥ ዜና

የኢትዮጵያን ታላቅነት የሚመጥን አየር ኃይል እየተገነባ ነው – ሌ/ጄነራል ይልማ መርዳሳ

By Adimasu Aragawu

November 06, 2025

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 27፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄነራል ይልማ መርዳሳ ከቢሾፍቱ ከተማ እና አካባቢው ነዋሪዎች ጋር 90ኛ ዓመት የአየር ኃይል የምስረታ ቀን አከባበርን አስመልክቶ ውይይት አድርገዋል።

ዋና አዛዡ በዚህ ወቅት የኢትዮጵያ አየር ኃይል በየዘመናቱ የሀገርን ሉዓላዊነት በማስከበር ረገድ አኩሪ ገድል መፈፀሙን ገልጸው÷ አሁንም የኢትዮጵያን ታላቅነት የሚመጥን ተቋም እየተገነባ መሆኑን አስታውቀዋል።

ዘንድሮ “የኢትዮጵያ አየር ኃይል የነፃነት እና የአንድነት ምልክት” በሚል መሪ ሐሳብ የምስረታ በዓሉን በተለያዩ ዝግጅቶች እንደሚያከብር አንስተው÷ የቢሾፍቱ ከተማና የአካባቢው ማህበረሰብ በዓሉን በጋራ ለማክበር በአንድነት መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል።

የምስረታ ቀኑ ለሀገርና ለተቋም ብሎም ለቢሾፍቱ ከተማ እድገትና የገፅታ ግንባታ የጎላ ሚና ያለው በመሆኑ ከተማውን በማፅዳት፣ በማስዋብና በማልማት እንዲሁም ፍፁም ሰላማዊ እንድትሆን ማድረግ የነዋሪዎች ኃላፊነት መሆኑንም አስረድተዋል።

ቀኑ በስፖርት ፌስቲቫል፣ በፓናል ውይይት፣ በአቪዬሽን ኤክስፖ በጉብኝትና በአየር ትርዒት እንደሚከበር ብርጋዲየር ጀኔራል ብሩክ ሰይፉ መግለፃቸውን የመከላከያ ኦንላይን ሚዲያ ለፋና ዲጂታል ገልጿል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!