አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 27፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ባህል ስፖርቶች ፌዴሬሽን አባል የሆነበትን የአፍሪካ ባህል ስፖርቶች ኮንፌዴሬሽን የአባልነት ማረጋገጫ ሰርቲፊኬት በዛሬው ዕለት ተሰጠው። የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት ወ/ሮ ህይወት መሃመድ ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ÷ ጥያቄው አስቀድሞ ተቀባይነት ማግኘቱን ጠቅሰው÷ በዚምባብዌ ሃራሬ ከተማ በተካሄደው ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ የማረጋገጫ ሰርቲፊኬት መረከባቸውን ተናግረዋል። አባልነቱ ከሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ጋር ድንበር ተሻጋሪ የሆነ ግንኙነቶችን በመፍጠር ባህላዊ ስፖርቶቻችንን ለማስተዋወቅ ይረዳል ብለዋል። በ1977 ዓ.ም የተመሰረተው የኢትዮጵያ ባህል ስፖርቶች ፌዴሬሽን የኢትዮጵያዊያን ባህላዊ ስፖርቶችና ጨዋታዎች በጥናትና ምርመር በመለየት ይዘታቸውን ጠብቀው ለትውልድ እንዲተላለፉ የማስተዋወቅ ስራዎችን እየሠራ ይገኛል። በሙባረክ ፋንታው
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!