አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 28፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአፋር ክልል ነዳጅ የመቀሸብ የወንጀል ድርጊት በመፈጸም የተጠረጠሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለዋል።
የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እንደገለጸው፤ በሰመራ ሎጊያ ከተማ ከጅቡቲ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ የነዳጅ ምርቶች ላይ ቅሸባ እንደሚፈጸምበት በተጠረጠረ ስፍራ ክትትል ተደርጓል።
በዚህም ክትትል ተደርጎ በተሰባሰበው መረጃ መሰረት ከአንድ የነዳጅ ጫኝ ተሸከርካሪ ቦቴ ነዳጅ በመቀነስ ሲሸጡና ሲገዙ የተገኙ 10 ተጠርጣሪ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው ነው።
በአካባቢው በሳጠራ ከተሰሩ 13 ቤቶች ውስጥ በነዳጅ የተሞሉ በርሜሎች እንደተከማቹ መገለጹን ያመለከተው መረጃው፤ እስካሁን በተደረገ ብርበራ 49 በርሜል ናፍጣ መያዙን ገልጿል።
ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ወሳኝ የሆነውን የነዳጅ ምርት ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት በመቀሸብ ለብክነት እና ለአደጋ በሚያጋልጥ ሁኔታ የአቅርቦትና ስርጭት ስራን ማስተጓጎል በነዳጅ ግብይት አዋጅ መሰረት ያስጠይቃል።
በሀገር ላይ የሚፈፀሙ የኢኮኖሚ አሻጥሮችን በመከላከል ጥፋተኞችን ተጠያቂ በማድረግ የነዳጅ ግብይቱን ሕጋዊ መስመር ለማስያዝ የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል ብሏል።
በመሳፍንት እያዩ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!