የሀገር ውስጥ ዜና

ሕይወት መሃመድ የአፍሪካ ባህል ስፖርቶች ኮንፌዴሬሽን ም/ፕሬዚዳንት ሆነው ተመረጡ

By Yonas Getnet

November 07, 2025

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 28፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ባህል ስፖርቶች ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ሕይወት መሐመድ የአፍሪካ ባህል ስፖርቶች ኮንፌዴሬሽን ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው ተመርጠዋል።

‎የአፍሪካ ባሕል ስፖርቶች ኮንፌዴሬሽን ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባዔ በዛሬው ዕለት ተጠናቅቋል፡፡

በዚህ ወቅትም ጉባዔው የኢትዮጽያ ባሕል ስፖርቶች ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት የሆኑትን ሕይወት መሐመድን ምክትል ፕሬዚዳንት አድርጎ በሙሉ ድምፅ መርጧል። ‌‎ የአፍሪካ ባሕል ስፖርቶች ኮንፌዴሬሽን የአባልነት ጥያቄን በይፋ ተቀባይነት ያገኘችው ኢትዮጵያ በቀጣይ ዓመት የመጀመሪያውን የአፍሪካ ባሕል ስፖርቶች ፌስቲቫል እንድታዘጋጅ ተመርጣለች፡፡

በዝምባብዌ ሐረሪ ‎ለ2 ቀናት የተካሄደው ጉባዔው አፍሪካን በባሕላዊ ስፖርቶች ለማስተሳሰርና አንድነት ለማጠናከር ያለመ መሆኑን ተመራጯ ሕይወት መሐመድ ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ተናግረዋል።

በሙባረክ ፋንታው

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!