የሀገር ውስጥ ዜና

የብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች በመዲናዋ የልማት ሥራዎችን እየጎበኙ ነው

By Adimasu Aragawu

November 08, 2025

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 29፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች በአዲስ አበባ ከተማ የተሰሩ የልማት ሥራዎችን እየጎበኙ ነው።

የአመራሮቹ ጉብኝት የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሙዚየም፣ የኢሬቻ ፓርክ፣ የአራዳ ፓርክ እና የላፍቶ የገበያ ማዕከልን ጨምሮ ሌሎች በከተማዋ የተሰሩ ሰው ተኮር ፕሮጀክቶችን ያካተተ መሆኑ ተገልጿል።

ፕሮጀክቶቹ መንግሥት የዜጎችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፍላጎቶችን በተገቢው መንገድ ለመመለስ የሚያደርገውን ጥረት የሚያሳዩ መሆናቸውም ተመላክቷል።

የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች በጉብኝቱ ወቅት መሬት ላይ በተተገበሩ ፕሮጀክቶች ፀጋን ለይቶ በማልማት ዜጎችን ተጠቃሚ ማድረግ እንዴት እንደሚቻል በተግባር እንዲመለከቱ ለማድረግ ያለመ እንደሆነ ተገልጿል።

የብልጽግና ፓርቲ የ2018 ዓ.ም ዓመታዊ የከፍተኛ አመራር ስልጠና በአዳማ ከተማ እየተሰጠ መቆየቱ ይታወቃል።

በአንዷለም ተስፋዬ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!