የሀገር ውስጥ ዜና

በመዲናዋ ህዝብን በማሳተፍ የተከናወኑ የልማት ተግባራት ውጤት አስገኝተዋል – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

By Adimasu Aragawu

November 08, 2025

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 29፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ ህዝብን በማሳተፍ የተከናወኑ የልማት ተግባራት ውጤት አስገኝተዋል አሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳር ከንቲባ አዳነች አቤቤ፡፡

የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች በአዲስ አበባ የኮሪደር እና የወንዝ ዳር ልማት፣ የቤት ልማት እና አቅርቦት ስራዎችን በመጎብኘት ላይ ናቸው፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዚህ ወቅት በመዲናዋ ህዝብን በማሳተፍ የተከናወኑ የልማት ተግባራት ውጤት ማጣታቸውበን ገልጸው÷ በዚህም አዲስ አበባን በአፍሪካ ተጠቃሽ ያደረገ ውጤቶች የተገኘበት ነው ብለዋል።

በቤት ልማትና አቅርቦት ላይ የግሉን ዘርፍ በማሳተፍ የተከናወኑ ስራዎች አቅርቦቱን ለማሳደግ ማስቻላቸውንም አመላክተዋል።

በተሰሩ ስራዎች በርካታ አቅመ ደካሞች ቤት ማግኘታቸውን የገለጹት ከንቲባዋ÷ በትምህርት ቤት ምገባ መርሐ ግብር ውጤት መገኘቱን ጠቅሰዋል፡፡

በመዲናዋ ህጻናትንና ወጣቶችን ታሳቢ ያደረጉ የስፖርት ማዘውተሪያ ቦታዎች ተገንብተው ለአገልግሎት ክፍት መደረጋቸውን አንስተው÷ መፍጠርና መፍጠን መርህን በመከተል ርብርብ እየተደረገ ነው ማለታቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው፡፡

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!