ስፓርት

ማንቼስተር ዩናይትድ እና ቶተንሃም አቻ ተለያዩ

By Mikias Ayele

November 08, 2025

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 29፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 11ኛ ሳምንት መርሐ ግብር የተገናኙት ማንቼስተር ዩናይትድ እና ቶተንሃም 2 ለ 2 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል።

በቶተንሃም ስታዲየም ዛሬ ቀን 9 ሰዓት ከ30 በተካሄደው ጨዋታ የቶተንሃም ሆትስፐር ግቦችን ቴል እና ሪቻልሰን ሲያስቆጥሩ፤ የማንቼስተር ዩናይትድን ደግሞ ምቤሞ እና ዴ ሊት አስቆጥረዋል።

የሊጉ ጨዋታዎች ምሽት 12 ሰዓት ቀጥሎ ሲካሄድ ኤቨርተን ከፉልሃም እንዲሁም ዌስትሃም ከበርንሌይ ይገናኛሉ፡፡

በሌላ የዛሬ ተጠባቂ መርሐ ግብር በሁሉም ውድድሮች ባለፉት ስምንት ጨዋታዎች ምንም ግብ ያልተቆጠረበት የሊጉ መሪ አርሰናል ወደ ስታዲየም ኦፍ ላይት አቅንቶ ምሽት 2 ሰዓት ከ30 በጥሩ ብቃት ላይ የሚገኘውን ሰንደርላንድ ይገጥማል፡፡

ስዊዘርላንዳዊው የቀድሞ መድፈኛ ግራኒት ዣካ የቀድሞ ክለቡን በተቃራኒ በሚገጥምበት የምሽቱ ጨዋታ የሰሜን ለንደኑ ክለብ መሪነቱን ለማጠናከር ወደ ሜዳ ይገባል፡፡

ቼልሲ አሰልጣኝ ጋሪ ኦኔልን ያሰናበተውን ዎልቭስን ምሽት 5 ሰዓት ላይ በስታምፎርድ ብሪጅ ያስተናግዳል፡፡